Quantcast
Channel: ዓለም
Viewing all articles
Browse latest Browse all 231

ወባን የማጥፋት ትሩፋት

$
0
0

 

በፒተር ቭሩማን

ከ1992 ዓ.ም. ወዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወባን በማጥፋት የተገኘው ስኬት ታሪካዊ የሚባል ሲሆን፣ በሒደቱም የአሜሪካ መንግሥት ወሳኝ ሚና ተጫውቷል፡፡ ከ1993 እስከ 2007 ዓ.ም. ባለው ጊዜ በመላው ዓለም በዋነኛነት ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ከአምስት ዓመት በታች የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 6.8 ሚሊዮን ሰዎችን በወባ ከመሞት ማዳን መቻሉን የዓለም የጤና ድርጅት ግምት ያሳያል፡፡

ነገር ግን ይኼ ስኬት በመላው ዓለም በየሁለት ደቂቃው አንድ ሕፃን በወባ በሽታ ከመሞት አላዳነም፡፡ በተያዘው ዓመት እጅግ የበዙት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች የሚወለዱ ሕፃናት የሆኑ ከ400 ሺሕ በላይ ሰዎች ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ ይኼ አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ የወባ በሽታ ሥርጭት ሰለባ ሲሆን፣ በ2007 ዓ.ም. በዓለም ላይ ከተመዘገቡ የወባ በሽታ ተጠቂዎች 90 በመቶውንና በወባ በሽታ ለሞት ከተዳረጉት ውስጥ 92 በመቶውን አስተናግዷል፡፡      

በኢትዮጵያ ወባን በመዋጋት የተገኘው ስኬት ከአምስት ዓመት በታች የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሕፃናትን ሞት በአስደናቂ ሁኔታ በመቀነስ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ ከ1997 ዓ.ም. እስከ 2008 ዓ.ም. በተደረገው የጋራ ጥረትና መንግሥት፣ ኅብረተሰቡ፣ ለጋሾችና አጋር ድርጅቶች በድምር በወሰዱዋቸው ዕርምጃዎች ይኼን ቁጥር በሕይወት ከሚወለዱት 1,000 ሕፃናት ውስጥ ከ123 በመቶ ሟቾች ወደ 67 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል፡፡ 

የዓለም የወባ ቀንን ሚያዝያ 17 ቀን ስናከብር፣ እስካሁን ባገኘናቸው ድሎች ይበልጥ እየተበረታታን ከሸሪኮቻችን ጋር በመሆን ወባን እስከናካቴው ለማስወገድ በትኩረት እንሠራለን፡፡ የአሜሪካ መንግሥት በተለይም በ1997 ዓ.ም. ይፋ በተደረገው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የወባ ኢኒሺየቲቭ (PMI) አማካይነት የወባ በሽታን በመዋጋት ረገድ ግንባር ቀደም ነው፡፡ መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች በሚገኙ 19 በመቶ የአፍሪካ አገሮች ይተገበራል፡፡ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (USAID) የሚመራው ይኼ መርሐ ግብር በአሜሪካ የበሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማዕከላት (CDC) ጋር በትብብር የሚተገበር ነው፡፡   

በአሜሪካ ፕሬዚዳንት የወባ ኢኒሺየቲቭ  አማካይነት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በበሽታው ከመያዝ የተጠበቁ ሲሆን፣ ሌሎች በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ደግሞ የወባ በሽታ ሕክምና ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በኢትዮጵያ በአሜሪካ ፕሬዚዳንት የወባ ኢኒሺየቲቭ አማካይነት 20 ሚሊዮን በፀረ ትንኝ መድኃኒት የተነከሩ የአልጋ አጎበሮች የተሠራጩ ሲሆን፣ ዘጠኝ ሚሊዮን ፈጣን የወባ መመርመሪያና ከ15 ሚሊዮን በላይ የወባ በሽታ ሕክምና መድኃኒት ተገዝቶ ሥራ ላይ ውሏል፡፡ ኢኒሺየቲቩ በወባ በሽታ መከላከል ዙሪያ የጤና ባለሙያዎችን አቅም የማሳደግ ሥልጠናም ይሰጣል፡፡ 

ወባን መቆጣጠር የሕፃናትን በሕይወት የመቆየት ዕድልና የእናቶችን ጤና ከማሻሻሉም በላይ፣ አስከፊ ድህነትን ለማጥፋትና በትምህርት ቤቶች የተሻለ ውጤት እንዲገኝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ ከሰሃራ በስተደቡብ በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ወባ አርሶ አደሮችን ከማሳቸው በማስቀረትና ሕፃናትን ከትምህርት በማስተጓጎል ድህነት እንዲስፋፋና የምግብ እጥረት እንዲባባስ ያደርጋል፡፡ ባለሙያዎች በዚህ የአኅጉሪቱ አካባቢ የወባ በሽታን ለመከላከል የሚውለው እያንዳንዱ ዶላር በምላሹ 60 ዶላር እንደሚያስገኝ ይገምታሉ፡፡   

በኢትዮጵያ የሚገኙ ጓደኞቼና የሙያ አጋሮቼ የወባ በሽታን  ለመዋጋት በየቀኑ ያለመታከት የሚሠሩ ቢሆንም፣ ከለጋሾች የሚገኘው ድጋፍ የታለመው ግብ ለመድረስ በቂ አይደለም፡፡ አዳዲስ የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎችንና ከግሉ ዘርፍ ጋር የበለጠ ቅርበት እንዲኖረን እንፈልጋለን፡፡ ወባን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ  ከኢትዮጵያ ብሎም ከዓለም ለማጥፋት ጥረቶችን ማቀናጀት ይኖርብናል፡፡

ወባን የመሰሉ በሽታዎችን መደምሰስ ትክክለኛውና ብልጫ ያለው ተግባር ነው!  

ከአዘጋጁ፡-ጸሐፊው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 231

Trending Articles